Recent News
የደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልላዊ መንግስት የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ክልላዊ ኮንፈረንስ በአርባምንጭ ከተማ ተካሄደ
በክልላዊ ኮንፈረንሱ ላይ የፌዴራል፣ የክልል፣ የዞን እና የልዩ ወረዳ አመራሮች ተሳትፈውበታል፡፡
የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፍሬህይወት አበበ በክልላዊ ኮንፈረንሱ ላይ እንደተናገሩት፣ በ2003 ዓ.ም በ13 ወረዳዎች የተጀመረው የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አገራዊ ትግበራ በአሁኑ ወቅት 770 ወረዳዎች ላይ የደረሰ ሲሆን፣ ከ32 ሚሊዮን በላይ ዜጎችም በጤና መድህኑ ታቅፈዋል፡፡
Read Moreየሩብ አመቱ የጋራ እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ውጤታማ ሆኖ ተጠናቀቀ
የኢትዮጵያ ጤና መድህን ኤጀንሲ ከኤጀንሲው ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ስራ አስኪያጆች፣ ከክልል ማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አስተባባሪዎች ፣ ከክትትልና ግምገማ ባለሞያዎች፣ ከአጋር አካላት ከመጡ ባለሙያዎች፣ እንዲሁም ከጤና ሚኒስቴር ፣ከኢትዮጵያ መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣንና ከመደሀኒት ፈንድ ተወካዮች በተገኙበት ከጥቅምት 3 – 5 በአዳማ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የበጀት ዓመቱ ሩብ ዓመት ስራ አፈፃፀም ግምገማ ውጤታማ ሆኖ ተጠናቋል።
Read Moreየኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ አመራሮች እና ባለሙያዎች በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልላዊ መንግስት የጨንቻ ወረዳን የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን የስራ እንቅስቃሴ ጎበኙ፡፡
በኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አለሙ አኖ የተመራው ቡድን ባደረገው የመስክ ጉብኝት የወረዳው የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ትግበራ አበረታች መሆኑን ተመልክቷል፡፡
Read Moreበማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ስርዓት ከ32 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ታቅፈዋል
የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ስርዓት (ማዐጤመ) በከተማና በገጠር መደበኛ ባልሆነው የኢኮኖሚ ዘርፍ ተሰማርቶ የሚገኘውን የህብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚ የሚያደርግ ሥርዓት ነው፡፡ ይህ የጤና መድህን ዓይነት በ2003 ዓ.ም በ13 ወረዳዎች በሙከራ ደረጃ በትግራይ፣ በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በደቡብ ብ/ብ/ህዝቦች ክልሎች ተጀምሮ ከሙከራ ወረዳዎች የተገኘውን ልምድ በመቀመር ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ እንዲስፋፋ ተደርጓል፡፡
Read Moreበድሬደዋ፣ በሀረሪ እና በሱማሌ ክልል ለሚገኙ የሚድያ አካላት ስልጠና ተሰጠ::
የጤና መድህን ጽንሰ ሀሳብና የሀገራት ተሞክሮ ፣ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን በኢትዮጵያ ያለበት ደረጃ እና ጤና መድህንን በሀገራችን ተደራሽ ለማድረግ ከሚድያ አካላት ምን ይጠበቃል በሚሉ ርእሶች ዙሪያ በድሬደዋ፣ በሀረሪ እና በሱማሌ ክልል ለሚገኙ የሚድያ አካላት ለሁለት ቀናት የቆየ ስልጠና በሀረር ከተማ ተሰጠ፡፡
Read More