ተልዕኮ፣ ራዕይ፣ ዓላማ
ተልዕኮ፣ ራዕይ፣ ዓላማ
የጤና መድህን ማለት ምን ማለት ነው?
የጤና መድህን አስቀድሞ በሚደረግ አነስተኛ መዋጮ ወይም ክፍያ ግለሰቦች ወይም ቤተሰቦች የጤና መታወክ ባጋጠማቸው ጊዜ ካልታሰበ ከፍተኛ የህክምና ወጪ የሚጠበቁበት ስልት ነው፡፡ የጤና መድህን በአነስተኛ የቅድመ ክፍያ ስልት መዋጮን በአንድ ቋት በማጠራቀም የዜጎችን የጤና አገልግሎት የማግኘት ዋስትናን በማረጋገጥ በገንዘብ እጦት ምክንያት በቂ ህክምና ያለማግኘት ስጋትንም የሚቀንስ ስርዓት ነው፡፡
የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ የፌዴራል መንግስት መስሪያ ቤት ሆኖ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 191/2003 የተቋቋመ ሲሆን
የኤጀንሲው ራዕይ
በ2035 ሁሉም የሀገሪቱ ዜጎች ፍትሃዊ እና ቀጣይነት ያለው የጤና መድህን ተጠቃሚ ሆነው ማየት፡፡
የኤጀንሲው ተልዕኮ
የጤና መድህን ስርዓትን ለማስፈፀም ቀልጣፋና ብቃት ያለው አሰራር በመዘርጋት፤ የአባላት መዋጮን በማሰባሰብና በማስተዳደር ሁሉን አቀፍ የሆነ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ሽፋን እና ተደራሽነት ቀጣይነት ባለው መልኩ ለዜጎች መሰጠቱን ማረጋገጥ፡፡
የኤጀንሲው እሴቶች
ታማኝነት፡- የጤና መድህን ስርዓቱ የተመሠረተበትን ዓላማ ማሳካት እንዲችል በትጋት ማገልገልና በቅንነት መስራት፤
ተጠያቂነት፡- የጤና መድህን ስርዓቱ አሰራር ህጋዊ መንገዶች ብቻ የተከተሉ እንዲሆኑ ማድረግ፣ ለወጡ ህጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች ተገዢ መሆን፤
አሳታፊነት፡- ባለድርሻ አካላት በጤና መድህን ሥርዓቱ ላይ አስተዋፅኦ ማድረግ እንዲችሉ ሁኔታዎችን ማመቻቸት፤
ግልፅነት፡- የጤና መድህን ስርዓቱን የፋይናንስ እና የአሰራር ሥርዓት ለሁሉም ባለድርሻ አካላት በየጊዜው ማሳወቅ፤
ቅድሚያ ለማህበረሰብ፡- በምንሰጣቸው አገልግሎቶች የማህበረሰቡን ፍላጎት ቅድሚያ ሰጥቶ መተግበር፡፡
የኤጀንሲው ዓላማ
የጤና መድህን ስርዓትን ማስፈፀም ነው፡፡