የፋይናንስና ኢንቨስትመንት ዳይሬክቶሬት
የፋይናንስና ኢንቨስትመንት ዳይሬክቶሬት
የፋይናንስና ኢንቨስትመንት ዳይሬክቶሬት የሚሰጣቸው አገልግሎቶች፡-
1. የኤጀንሲውን የፋይናንስ ግዢና ንብረት አስተዳደር እንዲሁም የኢንቨስትመንት ሥራዎችን ያቅዳል፣ ይመራል ይቆጣጠራል፤
2. የኤጀንሲውን ዓመታዊ በጀት መሰረት ባደረገ መልኩ የጥሬ ገንዘብ ፍላጎት ያዘጋጃል ጥያቄ ያቀርባል አፈፃፀሙን ይከታተላል፤
3. በኤጀንሲው ስር ለሚገኙ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ስራውን በተመለከተ የክትትልና ድጋፍ ስራዎችን ይሰራል፤
4. ጠንካራ የፋይናንስ አስተዳደር፣ የቁጥጥርና የክትትል ስርዓት ይዘረጋል፤
5. በመንግስት የፋይናንስ አስተዳደር ሕግ መሠረት የተሟላ የፋይናንስና የሂሳብ መዛግብት ይይዛል፤
6. የዳይሬክቶሬቱን የስራ መመሪያ ማኑዋሎች ያዘጋጃል፤ እንደአስፈላጊነቱ እንዲሻሻሉ ያደርጋል፤
7. የኤጀንሲውን የፋይናንስ አቅም ለማጎልበት አማራጭ የኢንቨስትመንት መስኮችን ይለያል፤ አዋጭነታቸውን በመገምገም በተመረጡ የኢንቨስትመንት መስኮች ላይ ይሳተፋል፤
8. ለጤና መድህን ስርዓቱ የሚያስፈልገውን የመጠባበቂያ ገንዘብ በመመሪያው መሰረት መያዙን ያረጋግጣል ውጤቱን ይከታተላል፤
9. የኤጀንሲውን የፋይናንስና ግዢና ንብረት አስተዳደር ስራዎች አፈፃፀም በተመለከተ ወቅታዊ ሪፖርቶችን ያዘጋጃል ለሚመለከታቸው አካላት ያቀርባል፤
10. የኤጀንሲውን የፋይናንስና የሂሳብ መዛግብት በየበጀት ዓመቱ መጨረሻ በመዝጋት የሂሳብ ሪፖርቶችን በውጪ ኦዲተሮች እንዲመረመር ያዘጋጃል ያደርጋል፤
11. የኤጀንሲው ንብረት ተመዝግቦ ስለሚያዝበትና አግባብ ባለው ሁኔታ ጥቅም ላይ የሚውልበትን ሥርዓት ይዘረጋል፤ ተግባራዊነቱን ይቆጣጠራል፤
12. የኤጀንሲው ንብረት ከብክነትና ሌሎች ጉዳቶች የሚጠበቅበትን ሁኔታ ያመቻቻል፤ ለታለመለት ዓላማ እንዲውል ያደርጋል፤
13. ማናቸውም ግዢዎች የመንግስትን የግዢ ሕግ በተከተለ ሁኔታ እንዲፈፀሙ ያደርጋል ይቆጣጠራል፤
14. ኤጀንሲው የሚፈለግበትን ማንኛውም የታክስ ግዴታውን በወቅቱ መወጣቱን ያረጋግጣል፤
15. በጤና መድህን ፈንድ የኢንቨስትመንት ስትራቴጂ ቀረፃና ትግበራ ላይ ይሳተፋል፤
16. የጤና መድህኑ ፖሊሲዎች፣ አሠራሮችና መመሪያዎች በቂ የውስጥ ቁጥጥር ስርዓት ያላቸው መሆኑን ያረጋግጣል፡፡