የደንበኞች እርካታ ማረጋገጫ ዳይሬክቶሬት

የደንበኞች እርካታ ማረጋገጫ ዳይሬክቶሬት የሚሰጣቸው አገልግሎቶች፡-

1. አባላት፣ አገልግሎት ሰጪዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በጤና መድህን ሥርዓቱ አፈፃፀም በተለይም በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያላቸውን አስተያየትና ቅሬታ በመመርመር ተገቢው መፍትሄ መሰጠቱን መከታተልና ማረጋገጥ፤

2. የደንበኞችን እርካታ ደረጃ ለማወቅ በየጊዜው የሚደረጉ የዳሰሳ ጥናቶችን ያስተባብራል፣ ይመራል፣ ውጤቶችን በወቅቱ ለበላይ ኃላፊ ያሳውቃል፤

3. ተቀባይነት ያላቸውን ግልፅና ቀላል የቅሬታ ማቅረቢያ መንገዶችን በመቀየስ (የቅሬታ ማቅረቢያ ቅጾችን በማዘጋጀት) ፣ ለውሳኔ በማቅረብ ተግባራዊነታቸውንም ማረጋገጥ፤

4. በደንበኞች እርካታና ቅሬታ አፈታት ዙሪያ ለአባላት፤ ለጤና ተቋማትና ለባለድርሻ አካላት ግንዛቤ መስጠት፤

5. የቅሬታ አፈታትን ዘመናዊ፣ ግልፅ፣ ፍትሃዊ እና ቀልጣፋ በማድረግ ለአባላት፣ ለጤና ተቋማትና ለባለድርሻ አካላት አገልግሎቱን ተደራሽ ማድረግ፤

6. የኤጀንሲው የቅሬታ ማቅረቢያ /መቀበያ/ ስርዓት ሁሉም ባለድርሻ አካላት እንዲያውቁት የሚያስችሉ ሥራዎችን መስራት፤

7. ከመደበኛ ቅሬታ ማቅረቢያ መንገዶች ውጪ በህብረተሰቡ፣ በተለያዩ የህትመትና ብሮድካስት ሚዲያዎች፣ በማህበራዊ ሚዲያዎችና በሌሎች መንገዶች በኤጀንሲው ሥራ ላይ የሚነሱ (የሚቀርቡ) ቅሬታዎችንና ችግሮችን መረጃ ሰብስቦ በመተንተን ተገቢውን ምላሽ ማዘጋጀትና ማሰራጨት፤ እንዲሁም የኤጀንሲን መልካም ገፅታ የሚገነቡ መረጃዎችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ከኮምንዩኬሽንና ሞቢይዜሽን ዳይሬክቶሬት ጋር ተባብሮ መስራት፤

8. በየጊዜው በሚቀርቡ ቅሬታዎች ላይ መወሰድ ስላለባቸው መፍትሄዎች እና እርምጃዎች ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመወያየት ችግሮቹ እንዳይደገሙና የአገልግሎት ጥራት ደረጃ እንዲሻሻል ማገዝ፤

9. የኤጀንሲው ሠራተኞች ስለ ደንበኞች እርካታና ስለ ኤጀንሲው የቅሬታ አያያዝ ሥርዓት እውቀት እንዲኖራቸውና ለተግባራዊነቱም አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ በተወሰነ ጊዜ ስልጠና መስጠት፣

10. በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የደንበኞች እርካታ ማረጋገጫ የሥራ ክፍሎች የስራ መመሪያ ማንዋሎች መሟላታቸውን ማረጋገጥ በየጊዜውም እንደአስፈላጊነቱ እንዲሻሻሉ ማድረግ፤