የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ስርፀት ዳይሬክቶሬት
የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ስርፀት ዳይሬክቶሬት
የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ስርፀት ዳይሬክቶሬት የሚሰጣቸው አገልግሎቶች፡-
1. እያንዳንዱ የኤጀንሲው ዋና ዋና ተግባራት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ ቀልጣፋና ውጤታማ እንዲሆን ያደርጋል፤
2. ለጤና መድህን ስርዓቱ አስፈላጊ የሆኑ ሶፍትዌሮችን የማበልፀግ ስራ መስራት፤ የማስተማር፤ ማስተባበርና ስራ ላይ ያውላል፤
3. የኤጀንሲው የመረጃ ሥርዓት ከሌሎች የጤናው ዘርፍ አካላት የመረጃ ስርዓት ጋር ለማዛመድ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን መምራት፣ ማስተባበር፣ ኤጀንሲው የተቀናጀ የኤሌክትሮኒክስ ኮሚዩኔኬሽን ሲስተም እንዲኖረው ማድረግ፤
4. የዕለት ተዕለት ስራዎችን፣ በየስራ ክፍሎች መካከል የሚኖር የመረጃ ልውውጥና ሌሎች ግንኙነቶችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዙ እንዲሆኑ ማድረግና መቆጣጠር፤
5. የጤና መድህን ስርዓቱ መረጃዎች በተዘጋጁት ሶፍትዌሮች እየተሰበሰቡ መሆኑን ማረጋገጥ፤
6. የዳይሬክቶሬቱን የስራ መመሪያ ማንዋሎችን ማዘጋጀት፤ በየጊዜውም እንደአስፈላጊነቱ እንዲሻሻሉ ማድረግ፤
7. በኤጀንሲው የሚካሄዱ የሲስተም ፕሮጀክቶችን ማስተባበርና መቆጣጠር፤
8. የኤጀንሲውን የመረጃ ስርዓት ወቅታዊነታቸውንና በአግባቡ መስራታቸውን ማረጋገጥ፤
9. የጤና መድህን ስርዓቱን የመረጃ ደህንነትና ሚስጢራዊነት ማረጋገጥና መቆጣጠር
10. የኤጀንሲውን ድረ ገፅ ማበልፀግና ማስተዳደር፤ ከሌሎች የስራ ክፍሎች የሚገኙ መረጃዎችን በኤጀንሲው የድረ-ገፅ አድራሻ ላይ መጫንና አስፈላጊውን ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ፤
11. የኤጀንሲውን የመረጃ መረብ ሲስተም፣ ንዑስ ሲስተሞችና ሰርቨሮች ይቀርጻል፤ ይዘረጋል፤ ለሥራ ዥግጁ ያደርጋል፣ ያስተዳድራል፣ይቆጣጠራል፤የመረጃ መረብ ሲስተም ላይ የሚፈጠሩ ችግሮችን ይፈታል፣ እንዲፈቱ ያደርጋል፣ ለኤጀንሲው ሰራተኞች በሶፍትዌሮች አጠቃቀም ዙሪያ ስልጠና ይሰጣል፣ የመረጃ መረብ ሲስተም ተጠቃሚዎችን ይቆጣጠራል፣ በኤጀንሲው ፖሊሲ መሰረት በየወቅቱ ባክአፕ ይወስዳል፣ ሲስተሙ በቫይረስ እንዳይጠቃ ማድረግ፤