የአገልግሎት ሰጪዎች ጉዳይ ጥራት ማረጋገጫ ዳይሬክቶሬት

የአገልግሎት ሰጪዎች ጉዳይ ጥራት ማረጋገጫ ዳይሬክቶሬት የሚሰጣቸው አገልግሎቶች፡-

1.  ለዳይሬክቶሬቱ ተጠሪ ለሆኑ የሥራ ክፍሎች የስራ መመሪያ ማንዋሎች መሟላታቸውን ያረጋግጣል፣ በየጊዜውም እንደአስፈላጊነቱ እንዲሻሻሉ ያደርጋል፤

2.  አገልግሎት ሰጪዎች የሚመረጡበትን መስፈርት እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤ አስፈላጊ መስፈርቶች መካተታቸውን ያረጋግጣል፤

3.  ከአገልግሎት ሰጪዎች ጋር ለሚደረግ የውል ስምምነት የሚያስፈልጉ ሰነዶችን እንዲዘጋጁ ያደርጋል፤ የተዘጋጁት ሰነዶች ብቁ መሆናቸውን ያረጋግጣል፤

4.  የጤና መድህን ስርዓቱን የህከምና ወጪ ዕድገት ለመቆጣጠር የሚያስችልና ለተጠቃሚው ጥራት እና አግባብነት ያለው አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የሜዲካል ኦዲት ስርዓት እንዲዘረጋ ያደርጋል፤ ለቅርንጫፎች በሜዲካል ኦዲት ዙሪያ እገዛ ያደርጋል፤

5.  በክፍያ ስልቶችና በክፍያ መጠን ዙሪያ የሚነሱ ጉዳዬችና ችግሮችን በማጥናት የመፍትሄ ሀሳብ ያቀርባል፣ በአዳዲስ የክፍያ ስልቶችና ስርዓቶች ላይ ጥናት ያደርጋል፣ ሥራ ላይ እንዲውል ሃሳብ ያቀርባል፤

6.  ጥራት ያለው የህክምና አገልግሎት ለማስፈን እንዲቻል ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የትብብር መድረኮችን በመፍጠር ይሰራል፤

7.  ለዳይሬክቶሬቱ ተጠሪ ለሆኑ የሥራ ክፍሎች የስራ መመሪያ ማንዋሎች መሟላታቸውን ያረጋግጣል፣ በየጊዜውም እንደአስፈላጊነቱ እንዲሻሻሉ ያደርጋል፤

8.  በየቅርንጫፉ የአገልግሎት ሰጪዎች ቁጥር በበቂ ደረጃ መሆኑን እና ጥራት ያለው አገልግሎት መቅረቡን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፤

9.  የአገልግሎት ሰጪዎችን ምልመላ፣ ምዝገባና የጥራት ቁጥጥር ሥራ በተገቢው መንገድ እየተከናወነ ስለመሆኑ ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፤

10.  የአገልግሎት ሰጪዎችን ክፍያ ኤጀንሲው ባፀደቀው የክፍያ ስልትና ተመን ስለመፈፀሙ ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፤

11.  በአገልግሎት ሰጪዎች መስፈርቶች ዙሪያ ጥናት ያደርጋል፤ እንደአስፈላጊነቱ የመሻሻያ ሃሳቦችን ያቀርባል፤

12.  ኤጀንሲው ለየቅርንጫፉ ያፀደቀው የአገልግሎት ሰጪዎች ክፍያ ተመን ወቅታዊነት በየጊዜው ያጠናል፣ ይከታተላል፣እንደአስፈላጊነቱ የመሻሻያ ሃሳቦችን ያቀርባል፤

13.  በአገልግሎት ሰጪዎች የክፍያ ስልቶችና የክፍያ መጠን ዙሪያ የሚነሱ ችግሮችና ጉዳዬችን በማጥናት የመፍትሄ ሀሳቦችን ያቀርባል፤

14.  የጤና መድህን አባላትና ተጠቃሚዎች አገልግሎት የሚያገኙበትን ከኤጀንሲው ጋር ውል በሚገቡ የጤና ተቋማት መደልደልና ማሳወቅ፤

15.  የጤና መድህኑ ተጠቃሚዎች የጤና አገልግሎት አጠቃቀምና የበሽታ ሁኔታ፤ ለጤና ወጪ የተከፈለ ክፍያ፤ እንዲሁም በጤና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የታዩ ችግሮችን መረጃ አደራጅቶ በመተንተን የመፍትሄ ሀሳቦችን ማቅረብ፡፡