የአባላት፣ ምዝገባና መዋጮ ጉዳይ ዳይሬክቶሬት

የአባላት፣ ምዝገባና መዋጮ ጉዳይ ዳይሬክቶሬት የሚሰጣቸው አገልግሎቶች፡-

1.  የጤና መድህን አባልነት የሚስፋፋበትን መንገድ ያቅዳል፣ ያጠናል፣ ተግባራዊ ያደርጋል፤ለጤና መድህን የሚደረገው መዋጮ ለኤጀንሲው የሚተላለፍበትን ስርዓት ይቀይሳል፤ በየጊዜው እንዲከለስ ያደርጋል፤

2.  የጤና መድህንን መተግበር ያለባቸው ተቋማት እና ማኅበረሰብ የጤና መድህን ስርዓቱ አባላት መሆናቸውን ያረጋግጣል፤

3.  የአባላትን መረጃ እንዲሰበሰብ ደርጋል፣ የተሰበሰበው መረጃ መተንተኑን ያረጋግጣል፤

4.  ለጤና መድህኑ የሚዋጣው መዋጮ በወቅቱና በሚፈለገው መጠን መሰብሰቡን ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፤

5.  አሠሪዎችና ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ መዋጮ በወቅቱ ማስተላለፋቸውን ይከታተላል፤

6.  አባላትና ተጠቃሚዎችን ለመመዝገብ የሚያስፈልጉ መረጃዎችን ይዘት ይወስናል፤ እንደአስፋለጊነቱም የመረጃው ይዘት እንዲከለስ ያደርጋል፤

7.  አባልነትን በተመለከተ ትግበራ ላይ የሚነሱ ጉዳዮችን ይዳስሳል፤ ለሚመለከታው አካል ማስተካከያ እንዲደረግ ሀሳብ ያቀርባል፤

8.  የአባላት ምዝገባ ዓላማ ባለቤት (Objective Owner) ሆኖ ያገለግላል፤ በምዝገባ መስክ በሀገሪቱ ያለውን የአፈጻጸም ሂደት ይከታተላል፣ ያስተባብራል፤

9.  የአባላትና ተጠቃሚዎች መታወቂያ ዝግጅትና ስርጭት የሚረዱ መረጃዎችን ያዘጋጃል፣ ወደ ሶፍትዌር ያስገባል ፤