የውስጥ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት

የውስጥ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት የሚሰጣቸው አገልግሎቶች፡-

1. በኤጀንሲው ውስጥ ጠንካራ የውስጥ ቁጥጥር ስርዓት መዘርጋቱን ያረጋግጣል፣

2. የኤጀንሲውን ዓመታዊ የኦዲት ዕቅድ ያዘጋጃል፣ ለውሳኔ ያቀርባል፤

3. የኤጀንሲውን የውስጥ ቁጥጥር ስርዓት በየጊዜው ይመረምራል፣ ይመዝናል፤ ብቃቱን ያረጋግጣል፤

4. በዳይሬክቶሬቱ ሥር ለተሸፈኑ የሥራ ክፍሎች በሙሉ የስራ መመሪያ ማንዋሎች መሟላታቸውን ያረጋግጣል፣ በየጊዜውም እንደአስፈላጊነቱ እንዲሻሻሉ ያደርጋል፤

5. የኤጀንሲው እንቅስቃሴዎች ከፖሊሲዎች፣ ከዓላማዎቹና ከአሰራር መመሪያዎቹ አንፃር በትክክል ስለመፈፀማቸው ይከታተላል፤

6. የውስጥ ቁጥጥር አገልግሎት ሥራዎችን ይመራል ይቆጣጠራል፣ የሚቀርቡለትን የውስጥ ቁጥጥር የምርመራ ፋይሎችንና ሪፖርቶችን ይመረምራል፣ ያረጋግጣል፤

7. የኦዲት አሰራር መመሪያዎች፣ አሠራሮችና ቅጾችን ያዘጋጃል፣በየጊዜውም እንዲሻሻሉ ያደርጋል፤

8. የኤጀንሲው የተለያዩ የሥራ ክፍሎችና ቅ/ጽ/ቤቶች የወጡትን ህጎችና መመሪያዎች አክብረው እየሠሩ መሆናቸውን ደረጃውን በጠበቀ የኦዲት አሠራር ይመረምራል፣ ይከታተላል፤

9. ኤጀንሲው ጠንካራ የውስጥ ቁጥጥር ስርዓት ሊኖረው በሚችልበት ሁኔታ ሁሉንም የሥራ ፍሎችን ያግዛል፤

10. የኤጀንሲው የፋይናንስና የንብረት እንቅስቃሴ በወጡ ህጎችና መመሪያዎች መሠረት መፈፀሙን ይመረምራል፣ ይከታተላል ያረጋግጣል፤

11. በየጊዜው የሚወጡ የፋይናንስ ሪፖርቶችን ትክክለኝነት ይመረምራል፣ ያረጋግጣል፤

12. የኦዲት ሥራ ሪፖርቶችን በየጊዜው ለመስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ ወይም በበላይ ኃላፊው በሚወከል ሰው ያቀርባል፤

13. በኦዲት ሥራ ወቅት የተገኙ የአሠራር ግድፈቶችን ጉድለቶችን በማጠናቀር ለእርማት ያቀርባል፣ ይከታተላል፤

14. ዓመታዊ የኤጀንሲው የንብረት ቆጠራ ወቅቱን ጠብቆ መካሄዱን ይከታተላል፤

15. በውጪ ኦዲተሮች የሚጠቆሙ የአሰራር ጉድለቶች እንዲታረሙ መደረጉን ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፤