የኮሙዩኒኬሽንና ሞቢላይዜሽን ዳይሬክቶሬት

የኮሙዩኒኬሽንና ሞቢላይዜሽን ዳይሬክቶሬት የሚሰጣቸው አገልግሎቶች፡-

1. የጤና መድህን ስርዓቱን በተመለከተ ከሚመለከታቸው የስራ ሂደቶች ጋር ተቀራርቦ በመስራት እንደአስፈላጊነቱ የተለያዩ ሚዲያዎችን/ መንገዶችን በመጠቀም ተከታታይነት ያለውን የህዝብ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን መስራት፣ ማስተባበርና መከታተል፤

2. የኤጀንሲው ቃል አቀባይ ሆኖ ያገለግላል፤

3. በዳይሬክቶሬቱ ስር ለተሸፈኑ የስራ ክፍሎች በሙሉ የስራ መመሪያ ማኑዋሎች መሟላታቸውን ያረጋግጣል፣ በየጊዜውም እንደአስፈላጊነቱ እንዲሻሻሉ ያደርጋል፤

4. ኤጀንሲው ከመገናኛ ብዙሀን ጋር የሚያደርገውን ግንኙነት ያስተባብራል፤ የኤጀንሲውን ተግባራት በመገናኛ ብዙሀን በቂ ሽፋን ማግኘታቸውን ያረጋግጣል፤

5. ለግንዛቤ ማስጨበጫ የሚያገለግሉ የተለያዩ በራሪ ጽሁፎችን እና ሌሎች ሰነዶችን ከሌሎች ክፍሎች ጋር በመተባበር ያዘጋጃል፤

6. በኤጀንሲው የሚካሄዱ ስብሰባዎችን፣ ወርክሾፖችን፣ ወዘተ… ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ያከናውናል፣ ያስተባብራል፣ ይመራል፤

7. የኤጀንሲው የፎቶግራፍ፣ የህትመት የኦዲዮና ቪዲዮ ቀረጻ ያከናውናል፣ መረጃዎቹንም በአግባቡ ያደራጃል፤

8. ኤጀንሲውን በተመለከተ በተለያዩ ሚዲያዎች (መንገዶች) የሚወጡ መረጃዎችን ይሰበስባል፣ ያደራጃል፣ እንደአስፈላጊነቱም ስለሁኔታው ለሚመለከታቸው ሀላፊዎች ሪፖርት ያቀርባል፤

9. በሌሎች ክፍሎች የሚዘጋጁ ዋና ዋና ጽሁፎች በይዘትና በቅርጽ ለህትመት ብቁ እንዲሆኑ አድርጎ ያሳትማል፣ ያሰራጫል፤

10. ወደ ኤጀንሲው የሚመጡ ደንበኞች ስለኤጀንሲው ማወቅ የሚፈልጉትን መረጃ እንደአግባብነቱ ይሰጣል፤

11. የጤና መድህን ስርዓቱ ላይ የሚሰሩ የህዝብ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ይሰራል፣ ያስተባብራል፤

12. የጤና መድህን ኤጀንሲው ከመገናኛ ብዙሀን ጋር የቅርብ ግንኙነት እንዲኖረው ያደርጋል፣ የጤና መድህን ስርዓቱ በበቂ የመገናኛ ብዙን ሽፋን እንዲያገኝ ይሰራል፣

13. በኤጀንሲው ሌሎች ክፍሎች የሚዘጋጁ ጽሁፎች ይሰበስባል ያደራጃል፣