የህግ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

የህግ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የሚሰጣቸው አገልግሎቶች፡-

1. ደንቦችና መመሪያዎችን ያረቃል፤ ከሌሎች የመንግስት አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎች ጋር መስማማታቸውን ይመረምራል፣ ያረጋግጣል፤

2. የጤና መድህን አባላት ቁጥር እንዲጨምር የሚያግዙ ረቂቅ ደንቦችንና መመሪያዎችን ያዘጋጃል፤

3. በዳይሬክቶሬቱ ስር ለተሸፈኑ የስራ ክፍሎች በሙሉ የስራ መመሪያ ማንዋሎች መሟላታቸውን ያረጋግጣል፣ በየጊዜው እንደአስፈላጊነቱ እንዲሻሻሉ ያደርጋል፤

4. ኤጀንሲው የሚዋዋላቸውን የውል ሰነዶች ያዘጋጃል፤

5. ኤጀንሲውን ወክሎ ይከሳል፣ መልስ ይሰጣል፣ ይከራከራል፤ በአጠቃላይ የፍርድ ቤት ጉዳዮችን ይከታተላል፤

6. የኤጀንሲው የስራ ክፍሎች (ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችን ) ጨምሮ ለሚገጥማቸው ህግ ነክ ጉዳዮች የህግ አስተያየት ይሰጣል፣ ያማክራል፤

7. ህግ ነክ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ዋና ዳይሬክተሩን ያማክራል፡፡