የሰው ሀብት ልማትና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

የሰው ሀብት ልማትና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የሚሰጣቸው አገልግሎቶች፡-

1. የኤጀንሲውን የሰው ሀይል ዕቅድ ስልጠናና ልማት እንዲሁም የንብረት አስተዳደር መምራትና መቆጣጠር፣

2. ኤጀንሲው ያለውን የሰው ሀይል ውጤታማ በሆነ መንገድ መጠቀሙን ማረጋገጥ ለዚሁም አስፈላጊ የሆኑ ሁኔታዎች መመቻቸታቸውን ማረጋገጥ፣

3. የኤጀንሲውን የሰው ሀይል ልማትና አስተዳደር ፖሊሲ ይቀርፃል፣ ያፀድቃል፣ተግባራዊ ያደርጋል፣

4. የኤጀንሲውን የሰው ሀይል ፍላጎት ዕቅድ ያዘጋጃል፣ ሲፀድቅ ተግባራዊ ያደርጋል፤

5. በዳይሬክቶሬቱ ስር ለተሸፈኑ የስራ ክፍሎች በሙሉ የስራ መመሪያና ማኑዋሎች መሟላታቸውን ያረጋግጣል፣ በየጊዜውም እንደአስፈላጊነቱ እንዲሻሻሉ ያደርጋል፣

6. የሠራተኞችን የቅጥር፣ የዕድገት፣ የዝውውርና የዲሲፕሊን ጉዳዮች በመንግስት ደንቦችና መመሪያዎች መሰረት መፈፀማቸውን ማረጋገጥ፣

7. የፐርሶኔል አገልግሎት ጥያቄዎችን ፈጣንና ቀልጣፋ ምላሽ እንዲያገኙ ያደርጋል፣

8. የኤጀንሲው የሰው ሀብት መረጃ በተሟላ ሁኔታ መያዙን ያረጋግጣል፣

9. ከየስራ ሂደቶች የሚቀርቡ የሥራ መግለጫዎችን በመተንተን የሥራ ምዘነ ያከናውናል፣

10. በውጤት ላይ የተመሠረተ የሥራ አፈፃፀም ግምገማ፣ የዕድገትና የደመወዝ ጭማሪ ስርዓት ያደራጃል፤ ይተገብራል፣

11. ኤጀንሲውና ሠራተኞቹ የዕለት ተዕለት ሥራዎቻቸውን ለማከናወን የሚያስፈልጋቸውን ቋሚና አላቂ ንብረት እንዲሁም ሌሎች አገልግሎቶች በሚፈለገው ደረጃ ተሟልተው መገኘታቸውን ያረጋግጣል፣ ይቆጣጠራል፤

12. የሰው ሀብት ልማት አስተዳደር ፍላጎትን መሠረት ያደረገ የሥልጠና ስርዓት በማደራጀትና በመተግበር ብቃትና ክህሎት ያለው ሰራተኛ እንዲኖር ያደርጋል፣