የቅርንጫፎች ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት
የቅርንጫፎች ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት
የቅርንጫፎች ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት የሚሰጣቸው አገልግሎቶች፡-
1. ከኤጀንሲው ቅርንጫፎች የሚቀርቡለትን ጥያቄዎች በመመርመር የተለያዩ የስራ ክፍሎችን በማነጋገር መፍትሔ እንዲያገኙ ያደርጋል፤
2. ቅርንጫፎች አስፈላጊውን ቴክኒካዊ እና አስተዳደራዊ ድጋፍ እንዲያገኙ ያደርጋል፤
3. በቅርንጫፎች አሰራር ዙሪያ ተቋማዊ መረጃ እንዲኖር ያደርጋል፤ ቅርንጫፎች ያሉባቸውን ችግሮች ለበላይ ኃላፊዎች በማቅረብ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ያደርጋል፤
4. ከሌሎች የስራ ክፍሎች ጋር በመተባበር የድጋፋዊ ክትትል ስራ ይሰራል፤በድጋፋዊ ክትትል ወቅት የታዩ ክፍተቶች መስተካከላቸውን ያረጋግጣል፤
5. በጤና መድህን ስርዓት ዙሪያ የሚወጡ ልዩ ልዩ መመሪዎችና የአሰራር ማንዋሎች ለቅርንጫፎች እንዲደርሱ ያደርጋል፤በትክክል ስራ ላይ መዋላቸውንም ያረጋግጣል፤፡፡
6. በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የተለያዩ አደረጃጀቶች እንዲቋቋሙ ማድረግና አደረጃጀቶችንም እንዲጠቀሙባቸው ማስተባበር፡፡
7. የጤና መድህን ስርዓት ውጤታማ እንዲሆን አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል ማድረግ፣
8. በቅርንጫፍ ጽ/ቤት ደረጃ ጠንካራ የክትትልና ግምገማ ስርዓት እንዲዘረጋ ማስተባበር እና መደገፍ፣