የፕላንና ጥናት ዳይሬክቶሬት

የፕላንና ጥናት ዳይሬክቶሬት የሚሰጣቸው አገልግሎቶች፡-

1. የኤጀንሲውን ስትራቴጂክ ዕቅድ ያዘጋጃል፣ እንዲጸድቅ ለበላይ አካል ያቀርባል፤

2. የኤጀንሲውን ዓመታዊ በጀት ያዘጋጃል፣ እንዲጸድቅ ለበላይ አካል ያቀርባል፤

3. በጤና መድህን ሥርዓቱ ዙሪያ የሚደረጉ ጥናቶችን ያቅዳል፣ ይመራል፣ እንዲከናዎን ያደርጋል፣ የጥናትና ምርምር ውጤቶች ተግባራዊ የሚሆኑበትን መንገድ ተከታትሎ ያስፈፅማል፤

4. የጤና መድህን ስርዓቱን ለኪሳራ ሊዳርጉ ከሚችሉና በአጠቃላይም በኤጀንሲው ዓላማና ተግባር ላይ አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ ስጋቶችን ለመከላከል አስፈላጊው የሪስክ ማኔጅመንት ሥራ መሰራቱን ያረጋግጣል፤

5. የተለያዩ የአገልግሎት ሰጪዎች የክፍያ ሥልቶችን በማጥናት የተሻሻሉ አሠራሮች እንዲተገበሩ ለውሳኔ ያቀርባል፤

6. በተለያዩ ክልሎች ያሉትን አገልግሎት ሰጪዎች የአገልግሎት ክፍያ ለመወሰን የሚያስችል የዋጋ ተመን ጥናት ይመራል፤

7. የጤና መድህን ስርዓቱን አጠቃላይ የስራ እና የፋይናንስ አፈጻጸም ይዳስሳል፣ይገመግማል፤

8. የጤና መድህን ስርዓቱን የጥቅም ማዕቀፍ በተመለከተ ጥናቶች እንዲካሄዱ ያደርጋል፤

9. ሁሉን አቀፍ በሆኑ የጤና መድህን እንቅስቃሴዎች ዙሪያ የተዘጋጁ ትንታኔዎችን ይገመግማል፣ የግምገማውን ውጤት ለበላይ አካል ያቀርባል፤

10. በኤጀንሲው እንቅስቃሴዎች ዙሪያ ጠንካራ የክትትልና ግምገማ ስርዓት ይዘረጋል፣ ተግባራዊ ያደርጋል፤ ይቆጣጠራል፤

11. የጤና መድህን ስርዓቱን እንቅስቃሴዎች ለመከታተልና ለመገምገም የሚረዱ መለኪያዎችና መሳሪያዎች እንዲዘጋጁ ያደርጋል፤

12. በየጊዜው የሚያስፈልጉ የዳይሬክቶሬቱን የስራ አፈፃፀምና ሌሎች ሪፖርቶችን ያዘጋጃል፤

13. በተለያዩ የክፍያ ስልቶች፣ በአገልግሎት ሰጪዎች ክፍያ ተመን፣ በጥቅም ማዕቀፉ ውስጥ ሊካተቱ ስለሚችሉ አዳዲስ የህክምና አገልገሎቶችና የጥቅም ማሻሻያዎች ወዘተ ላይ የሚደረጉ ጥናቶችን ያስተባብራል፣ ይመራል፤

14. በኤጀንሲው የሪስክ ማኔጅመንት ስትራቴጂና መመሪያ ቀረፃ ከሌሎች የየሥራ ክፍሉ ኃላፊዎች ጋር በመሆን ይሰራል፣ ተግባር ላይ መዋሉን ያረጋግጣል፤

15. በኤጀንሲው ዓላማና ተግባር ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ሊያስከትሉ የሚችሉ ስጋቶችን ይለያል፣ ያጠናል፤

16. የስጋቶችን የተፅእኖ መጠን ይመዝናል፣ በኤጀንሲው ፖሊሲና መመሪያ መሠረት ደረጃቸውን ይመድባል፣ በየጊዜው የሚኖሩ ለውጦችን እየተከታተለ ደረጃቸውን እንደአግባቡ ያስተካክላል፤

17. በኤጀንሲው ዓላማና ተግባር ላይ ስላሉ ስጋቶች በየደረጃው ለሚገኙ የሥራ ኃላፊዎችና ክፍሎች እንደየአግባቡ ሪፖርት ያደርጋል፤

18. በኤጀንሲው ዓላማና ተግባር ላይ ስላሉ ስጋቶች ከሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመመካከር ስጋቶቹ ስለሚቀንሱበት ወይም ደግሞ ወደ ሌላ የሪስክ ተሸካሚ ተቋም ሊተላለፉ ስለሚችሉበት ሁኔታ ያጠናል፣ ይሰራል፤

19. ጠንካራ የኮርፖሬት ገቨርናንስ ስርዐት እንዲሰፍን ጥረት ያደርጋል፤

20. የኤጀንሲው ፖሊሲዎችና መመሪያዎች በሚገባ ሥራ ላይ መዋላቸውን ከውስጥና ከውጭ ኦዲተሮች ጋር በመገናኘት ጭምር ይመረምራል፤

21. የኤጀንሲው ሰራተኞች ስለስጋቶቹ ያላቸውን ዕውቀት ከፍ ለማድረግ ትምህርት፣ ስልጠናና ድጋፍ ይሰጣል፤

22. በሥራ ክፍሉ እንቅስቃሴ ላይ በየወቅቱ ረፖርት እያዘጋጀ ያቀርባል፤

23. የኤጀንሲውን የሪስክ ማኔጅመንት ስትራቴጂና መመሪያ በየሥራ ክፍሉ በሚገባ ተግባር ላይ መዋላቸውን ይከታተላል፤በየሥራ ክፍሎቹ የሚታዩ ድክመቶችን ሪፖርት ያደርጋል፤

24. የኤጀንሲው የሪስክ ፖሊሲና መመሪያዎች እንደተጠበቁ ሆነው የሚከሰቱ አደጋዎችና ጉዳቶች መነሻ ምክንያቶችና ወደፊት እንዳይደገሙም ሊወሰዱ ስለሚገባቸው እርምጃዎች እያጠና ሪፖርት ያደርጋል፤

25. በየሥራ ክፍሉ ያለውን የሪስክ ማኔጅመንት መመሪያዎች አፈፃፀም መረጃ ይሰበስባል፣ የሚታዩ ድክመቶችን ሪፖርት ያደርጋል፤

26. በኤጀንሲው ውስጥ የሚከሰቱ አደጋዎች የሚያስከትሏቸው ጉዳቶችና ኃላፊነቶች መጠን ዝርዝር መረጃና ስታቲስቲክስ ይይዛል፣ በየወቅቱም እያቀናበረ ሪፖርት ያደርጋል፤

27. በኤጀንሲው ዓላማና ተግባር ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ሊያስከትሉ በሚችሉ ስጋቶች ላይ የሚወጡ መረጃዎችን እያጠናቀረ ይይዛል፣ በስጋቶች ላይ በሚደረጉ ጥናቶች ላይ ያግዛል፤

28. ኤጀንሲው በሚጠቀምባቸው የስጋት ማስወገጃ/መቆጣጠሪያ መንገዶች ውጤታማነት መረጃ ይሰበስባል፣ ይተነትናል፤

29. የጤና መድህን ስርዓቱን አፈጻጸም ውጤታማነት ይገመግማል፣ ለአፈጻጸሙ መሻሻል የሚረዱ መፍትሄዎችን ይሰጣል፤

30. በሁሉም የኤጀንሲው የሥራ ክፍሎች የአፈጻጸም መለኪያ ስርዓት እንዲዘረጋ ድጋፍ ይሰጣል፤