የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ የተቀናጀ ድጋፋዊ ጉብኝት ሊያደርግ መሆኑ ተገለጸ
የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ የተቀናጀ ድጋፋዊ ጉብኝት ሊያደርግ መሆኑ ተገለጸ
የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ ዋናው መስሪያ ቤት ሀላፊዎችና የሚመለከታቸው ባለሞያዎች የኤጀንሲው ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጆች የክልል ጤና ቢሮ አሰተባባሪዎች የዞንና የወረዳ ማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አስተባባሪዎች እንዲሁም ከክሊንተን ሄልዝ ኢኒሸቲቭ የተውጣጡ ባለሞያዎችን ያሳተፈ በዘጠኝ ቡድን በመደራጀት ከታህሳስ 27/2011 ጀምሮ በአራቱ ክልሎች የሚገኙ የጤና መድህን ዝግጅት ስራዎችን ለመደገፍ እንደሚንቀሳቀስ ታውቋል፡፡
የድጋፋዊ ጉብኝቱን አላማ አስመልክቶ የኢትዮጵያ ጤና መድህን ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለሙ አኖ በሰጡት ማብራሪያ የተቀናጀ ድጋፋዊ ጉብኝቱ በበጀት አመቱ በእቅድ በተያዘው መሰረት በ2011 የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን የአባላትና ምዝገባና እድሳት ስራዎች ላይ ኤጀንሲውና ክልሎች በእቅድ የያዙትን የአባልነትና የእድሳት ሽፋን በእቅዱ መሰረት እንዲሳካ ስራው ከመጀመሩ በፊት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ ድጋፍ በማድረግ የጤና መድህን ስርዓአቱን ውጤታማ ሆኖ እንዲቀጥል ነው ብለዋል፡፡
በተቀናጀ ድጋፋዊ ጉብኝት የሚሸፈኑ ቦታዎችን አሰመልክቶ ሲናገሩ የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን በተተገበረባቸው አራቱ ክልሎች ማለትም በአማራ፣ ትግራይ፣ ኦሮሚያ እና በደቡብ ሲሆን የጤና መድህን ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችም ያሉበት ሁኔታም ይጎበኛል ብለዋል፡፡ አቶ አለሙ አክለው እንደገለጹት በድጋፋዊ ጉብኝቱ በአጠቃላይ 38 የማህበረሰብ ጤና መድህን ወረዳዎችና 15 የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ይጎበኛሉ ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ጤና መድህን ኤጀንሲ ሁለት የጤና መድህን ሥርዓት ዓይነቶች ትግበራና አፈጻጸምን ለመምራት፣ ለማስተባበርና ለመከታተል በሚኒስትሮች ምክር ቤት የተቋቋመ ተቋም ሲሆን ዋና ዓላማውም የጤና መድህን ሥርዓትን በአገራችን ተግባራዊ በማድረግ የጤና ወጪ በህብረተሰቡ የሚያስከትለውን ጫና በመቀነስ ፍትሃዊ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን እና የጤና አጠቃቀምን ማጎልበት ነው፡፡
እንዲቀጥል ለማድረግ ነው ብለዋል፡፡