ውጤታማና ዘላቂነት ያለው የጤና መድህን ስርአት ለመዘርጋት የሚዲያ ባለሙያዎችና በየደረጃው ያሉ የፖለቲካ አመራሮች ላይ ትኩረት ሰቶ መሰራት እንዳለበት ተጠቆመ

ውጤታማና ዘላቂነት ያለው የጤና መድህን ስርአት ለመዘርጋት የሚዲያ ባለሙያዎችና በየደረጃው ያሉ የፖለቲካ አመራሮች ላይ ትኩረት ሰቶ መሰራት እንዳለበት ተጠቆመ

የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በአክሱም ከተማ ያሬድ ዜማ ሆቴል ከትግራይ ክልል ለተውጣጡ ጋዜጠኞችና የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ባዘጋጀው የግንዛቤ ፈጠራ ስልጠና ላይ ሰልጣኞቹ እንዳሉት የፖለቲካ አመራሮችና ጋዜጠኞች በቁርጠኝነትና በሀገራዊ ስሜት ከሰሩ በህብረተሰቡ ዘንድ ካላቸው ቁርኝት የተነሳ በቀላሉ የህዝቡን ግንዛቤ ለማሳደግ አይነተኛ መንገድ በመሆኑ በሌሎች ሀገራት የሚታየውን አይነት ውጤታማና በቀጣይነቱም አስተማማኝ የጤና መድህን ስርአት ለማስፈን ያስችላል ብለዋል 

የጤና መድህን ጽንስ ሃሳብና የአገራት ተሞክሮ ምን እንደሚመስል የመወያያ ጽሁፍ ያቀረቡት የህዝብ ግንኙነት ባለሙያው አቶ ኢዮብ ገላዬ በአለም ላይ ካሉት የጤና መድህን አይነቶች በፍላጎት ላይ የተመሰረተና መደበኛ ባልሆነው ክፍለ ኢኮኖሚ ላይ ለተሰማሩት የህብረተሰብ ክፍሎችን የሚያካትተውን የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አይነት በስፋት የዳሰሱ ሲሆን በዚህ የጤና መድህን አይነት ውጤት ያስመዘገቡ አገራትንም በመጥቀስ የኛም አገር ይህን ማድረግ እንደማይሳናት ጠቅሰው የሚዲያ ባለሙያዎች ድርሻ ወሳኝ በመሆኑ የበኩላቸውን እንድወጡም ጥቀዋል
የጤና መድህን ስርአት በመላው አገራችን ለማስፋፋትና ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ከጋዜጠኞችና ከሚዲያ ባለሙያዎች ጋር እንደት እንደሚሰሩ የመነሻ ጽሁፍ ያቀረቡት ደግሞ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዘመድኩን አበበ ሲሆኑ የሚዲያ ባለሙያ በመረጃ ህዘብን መቅደም እንዳለበትና የህዝብን ጥቅም ማስቀደምና አደጋን መቀነስ ተግባሩ ስለሆነ ጤናማ ማህበረሰብ እንድፈጠር በሙያቸው የበኩላቸውን ድርሻ እንድወጡ ጠይቀው ጋዜጠኞች ድምጽ ለሌላቸው ዜጎች ድምጽ በመሆን ወጥነት ያለው የጤና መድህን ስርአት እንድኖር የበኩላቸውን እንድወጡም አደራ ብለዋል፡፡

የጤና መድህን ሂደትና ማህረሰብ አቀፍ የጤና መድህን በአገራችንና በክልል ደረጃ አሁን ያለበትን ሁኔታ ያቀረቡት በኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ የመቀሌ ቅርንጫፍ ኃላፊ አቶ አረጋዊ በላይ የጤና መድህን ስርአት በአገራችን በቅርብ ጊዜ የተጀመረ ቢሆንም አሁን መልካም ውጤት እንዳላስበዘገበ ጠቅሰው የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህንም ቢሆን በትግራይ ክልል በአጻጸምና አባላትን በማፍራት ከዞን ዞንና ከወረዳ ወረዳ ቢለያይም በአጠቃላይ ሲታይ ጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝና ለዚህም ውጤት የጋዜጠኞችና የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ሚና ቀላል አይደለም ወደፊትም ትብብራቸው እንዳይለያቸው ጥሪ አቅርበው ስልጠናው መጠናቀቁን ለመረዳት ችለናል፡፡

Source: 
Ethiopian Health Insurance Agency