የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ የቀጣይ አምስት አመት ስትራቴጂክ እቅድ ላይ ውይይት ተካሄደ
የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ የቀጣይ አምስት አመት ስትራቴጂክ እቅድ ላይ ውይይት ተካሄደ
የኢትዮጵያ ጤና መድህን ኤጅንሲ በቀጣይ አምስት አመት ሊመራበት ባዘጋጀዉ ረቂቅ ስትራቴጂክ እቅድ ላይ የክልል ጤና ቢሮ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አስተባባሪዎች፣ ከኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ ጋር የሚሰሩ አጋር አካላት እንዲሁም የኤጀንሲዉ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጆች ጋር በአዳማ ከተማ ውይይት አካሂዷል፡፡
የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሚዛን ኪሮስ የውይይት መድረኩን በንግግር ሲከፍቱ እንዳሉት፣ ኤጀንሲው ባለፉት አምስት አመታት የተመራበት ስትራቴጂክ እቅድ አፈፃፀም ከተቋሙ ውጪ ባሉ አካላት እንዲገመገም ተደርጓል፡፡
ያለፉትን አምስት አመታት ጠንካራ ጎኖችና ውስንነቶች መሰረት በማድረግ የኤጀንሲው ቀጣይ አምስት አመታት ረቂቅ ስትራቴጂክ እቅድ መዘጋጀቱን ጠቁመው፣ በኤጀንሲው ባለድርሻ አካላት በስፋት ከተመከረበት በኋላ ሙሉ ሰነድ ሆኖ ይወጣልም ብለዋል፡፡
የውይይት መድረኩ ተሳታፊዎችም አዲስ በተዘጋጀው ረቂቅ የአምስት አመት ስትራቴጂክ እቅድ ላይ የኤጀንሲው ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ እሴቶች ስትራቴጂክ ቴሞች እና ኢኒሼቲቮች ላይ በቡድን እና በጋራ በመሆን ለሶስት ቀናት በመምከር ስትራቴጂክ እቅዱን በግብአት አዳብረዋል፡፡
የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ የቀጣይ አምስት አመት ስትራቴጂክ እቅድ በቀጣይም ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር ይደረግበታል፡፡