የሩብ አመቱ የጋራ እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ውጤታማ ሆኖ ተጠናቀቀ
የሩብ አመቱ የጋራ እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ውጤታማ ሆኖ ተጠናቀቀ
የኢትዮጵያ ጤና መድህን ኤጀንሲ ከኤጀንሲው ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ስራ አስኪያጆች፣ ከክልል ማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አስተባባሪዎች ፣ ከክትትልና ግምገማ ባለሞያዎች፣ ከአጋር አካላት ከመጡ ባለሙያዎች፣ እንዲሁም ከጤና ሚኒስቴር ፣ከኢትዮጵያ መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣንና ከመደሀኒት ፈንድ ተወካዮች በተገኙበት ከጥቅምት 3 – 5 በአዳማ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የበጀት ዓመቱ ሩብ ዓመት ስራ አፈፃፀም ግምገማ ውጤታማ ሆኖ ተጠናቋል።
በዘህ የግምገማ መድረክ ላይ ተሳታፊዎች በንቃት በመሳተፍ በርካታ የማዳበሪያ ሀሳቦችን ሰጥተዋል። በጉባኤው ማጠቃለያ ላይ የ2013 ዓ/ ም የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን የማቀጣጠያ ሰነድ እና የ2013 ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች በአቶ ጉደታ አበበ የኢትዮጵያ ጤና መድህን ኤጀንሲ የአባላትና መዋጮ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ቀርቦ በተሳታፊዎቹ የማዳበሪያ ሀሳብ ተሰጦባቸዋል። ከተሰጡት ሀሳቦች መካከል በንቅናቄ ስራው የአጋር አካላትን ብናሳትፍ፣ የንቅናቄ ስራው መጪውን የሀገሪቱ ዋና ዋና ስራዎችን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ቢቃኝ የሚሉ ይገኙበታል።
በጉባኤው ማጠቃለያ ላይ የኢትዮጵያ ጤና መድህን ኤጄንሲ ዋና ዻይሬክተር ወ/ሮ ፍሬህይወት አበበ ባሰተላለፉት መልዕክት በጉባኤው የተነሱትን ማዳበሪያ ሀሳቦችን ኤጀንሲው ወሰዶ እንደሚጠቀምባቸው ለተሳታፊዎቹ ገልፀው፣ በተለይም ለንቅናቄ ስራው በየደረጃው ያሉ የመገናኛ ብዙሃንን እና የህዘብ ክንፍን መጠቀም በጣም አስፈላጊ መሆኑን አስመረውበታል።
በመጨረሻም በጉባኤው ስምምነት የተደረሰባቸው ስራዎች በጊዜ የተከፋፈለ የድርጊት መርሀ ግብር ወጥቶላቸው ወደ ስራ እንዲገባ ስምምነት ላይ ተደርሶ ለሶስት ቀናት ሲካሄድ የቆይው የሩብ ዓመቱ የጋራ ግምገማ መድረክ ተጠናቋል ፡፡